ስለ እኛ

Home / About

እኛ ማን ነን?

ስለ ፋምዝ የሕፃናት ማቆያ

“የልጆችዎ ሁለተኛ ቤት!”

ፋምዝ የህፃናት መዋያና ማቆያ በአዲስ አበባ ከተማ አያት አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፤ ልጆችን በእናትነት እቅፍና በታላቅ ርህራሄ በመንከባከብ፣ በምቾትና በደህንነት የሚያሳድግ የልጆች ሁለተኛ ቤት ነው። ማዕከላችን ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ተመስርቶ የአገልግሎት ጉዞውን የጀመረ ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም ወላጆች ስለልጆቻቸው ቅንጣት ስጋት ሳይሰማቸውና ወዲህ ወዲያ ሳይሉ የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን በሙሉ ሰላም እንዲያከናውኑ ማገዝ ነው። ልጆችም በስነ-ምግባር የታነጸ ሁለንተናዊ ስብዕና እንዲኖራቸው በትጋት እንሰራለን።

ማዕከላችን በአያት ክፍለ ከተማ፣ በፍሬሽ ኮርነር መንገድ (ዞን 6) የሚገኝ ሲሆን፤ ሁሉንም የመንግስት መመሪያዎች አሟልተን፣ በሙሉ ህጋዊነትና በስርዓት ነው የምንሰራው።

ለልጆች ምቹ፣ ሰላማዊ እና ደረጃውን የጠበቀ የመማሪያና የመጫወቻ ስፍራ በማዘጋጀት፣ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን በታላቅ ኃላፊነት እያሳደግን እንገኛለን።

ተልዕኳችን

የኛ ትልቁ ዓላማ ልጆቻችን በፍቅርና በስነ-ምግባር ታንጸው፣ በእናትነት እቅፍ ውስጥ እንዲያድጉ ማድረግ ነው። ልጆች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ባህላቸውን አውቀውና ትምህርት ወደው ለቁምነገር እንዲበቁ እንጥራለን። እያንዳንዱ ልጅ በራሱ የሚተማመንና ቤተሰቡን አክባሪ ሆኖ እንዲያድግ እናደርጋለን፤ ወላጆችም ስለልጆቻቸው ምንም ሳይሰጉ ስራቸውን በሰላም እንዲያከናውኑ በታማኝነት ከጎናቸው እንቆማለን።

ራዕያችን (Our Vision)

በፋምዝ የህፃናት መዋያና ማቆያ የሚያድጉ ልጆች ነገ ላይ፦

  • በራሳቸው የሚተማመኑና ለእውቀት ንቁ የሆኑ

  • ለወላጅና ለማህበረሰቡ ትልቅ ክብር ያላቸው

  • በማንነታቸውና በባህላቸው የሚኮሩ

  • በአካልም ሆነ በአእምሮ ጠንካራ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ::

የረጅም ጊዜ ህልማችንም፣ የአዲስ አበባ ወላጆችንና የልጆቻቸውን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ ማዕከላችንን በየጊዜው በዘመናዊ መሣሪያዎችና አሰራሮች እያደስን፣ ልጆች በሁለንተናዊ መልኩ የሚታነጹበት ቀዳሚና ተመራጭ የልጆች ማረፊያ ሆኖ መቀጠል ነው።

ልዩ የሚያደርገን ምንድን ነው?

ፋምዝ የህፃናት መዋያና ማቆያ ተራ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን፣ ልጆች በሁለንተናዊ እውቀትና ስብዕና የሚታነጹበት ማዕከል ነው። ከወትሮው የተለየና ልጆችን ለቁምነገር የሚያበቁ ልዩ አገልግሎቶቻችን፦

  • የባህልና የማንነት ትምህርት፦ ልጆች ገና በለጋነታቸው የሀገራቸውን ባህልና እሴት አውቀው እንዲያድጉ እናደርጋለን።

  • የበገና ትምህርት፦ መንፈስን የሚያድስና ትዕግስትን የሚያስተምረውን ባህላዊ የበገና መሳሪያ ትምህርት እንሰጣለን።

  • የቴይኳንዶ (Taekwondo) ስልጠና፦ ለልጆች ቅልጥፍና፣ ለአካል ጥንካሬና ለራስ መከላከያ እንዲረዳቸው በባለሙያ እናሰለጥናለን።

  • ምቹ የአገልግሎት ሰዓታት፦ እንደ ወላጆች ፍላጎት በሙሉ ቀን ወይም በግማሽ ቀን አገልግሎት እንሰጣለን።

  • የወላጆች ምክክርና ክትትል፦ ስለ እያንዳንዱ ልጅ ሁኔታና እድገት ከወላጆች ጋር በቅርብ እየተመካከርን ልዩ እንክብካቤ እናደርጋለን።

እሴቶቻችን (Our Values)

  1. ልጅን እንደ ልጅ መያዝ፦ እኛ ጋር የመጣን እያንዳንዱን ልጅ ልክ እንደ ገዛ ልጃችን ነው የምናየው። በትዕግስትና በፍቅር እያቀፍን፣ ክብራቸውን ጠብቀን እናሳድጋቸዋለን።
  2. አስተማማኝ ቦታ፦ ቦታው ንጹህና ሰላም ስለሆነ፣ ወላጆች ልጃቸውን እኛ ጋር ጥለው ሲሄዱ፣ ልባቸው አርፎ ስራቸውን እንዲሰሩ እናደርጋለን።
  3. ባህልና ጨዋነት፦ ልጆቻችን የሀገራቸውን ባህልና ጨዋነት ገና በለጋነታቸው አውቀው፣ በማንነታቸው እንዲኮሩ ነው የምናደርገው።
  4. ጥሩ ፀባይና ራስን መቻል፦ ልጆች በመልካም ፀባይ እንዲታነጹ፣ በራሳቸው እንዲተማመኑና የራሳቸውን ነገር መቻል እንዲለምዱ በደንብ እንከታተላቸዋለን።
  5. ከወላጅ ጋር መመካከር፦ የልጁን ሁኔታ ለማስተካከልና ውጤታማ ለማድረግ፣ ከወላጅ ጋር እንደ ቤተሰብ በቅርብ መነጋገርና መመካከር የሁልጊዜ መመሪያችን ነው።

የመማሪያ አካባቢያችን

የማዕከላችን ቅጥር ግቢ፦

  • ሁልጊዜም ንጹህና የተስተካከለ፦ ልጆች በንጽህና እንዲቆዩና ምቾት እንዲሰማቸው በደንብ የተደራጀ ነው።

  • ልጆችን የሚስብና ለጨዋታ የሚጋብዝ፦ እያንዳንዱ ክፍል ልጆች በደስታ እንዲውሉና እንደ ቤታቸው እንዲሰማቸው ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።

  • በስርዓት የተመራ ግን ደግሞ ነጻነት ያለው፦ የልጆችን ፍላጎትና የዕድሜ ደረጃ ከግምት ውስጥ ያስገባ የትምህርትና የጨዋታ ጊዜ አለን።

  • የእያንዳንዱን ልጅ ችሎታ የሚያበረታታ፦ ልጆች በተለያዩ መንገዶች እውቀት እንዲቀስሙና ጎበዝ እንዲሆኑ ይደረጋል።

በማዕከላችን ውስጥ ልጆች የሚያድጉት በታታሪና ለልጆች ልዩ ፍቅር ባላቸው ባለሙያዎች እጅ ሲሆን፣ ከትምህርታቸው ባሻገር ለደስታቸውና ለስነ-ልቦናቸው ትልቅ ትኩረት እንሰጣለን።

ለወላጆች ያለን ቃል

ልጅን ለሰው መስጠት ትልቅ ውሳኔ እንደሆነ እንረዳለን። ለዚህም ነው እኛ ጋር ስትመጡ የሚከተሉትን ቃላት የምንገባው፦

  • ሁልጊዜም ዝግጁ ነን፦ ስለ ልጃችሁ ውሎም ሆነ ስለማንኛውም ነገር በፈለጋችሁት ሰዓት በግልጽ እንነጋገራለን።

  • ግልጽነት መመሪያችን ነው፦ በማዕከላችን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎትና የምናደርገው እንክብካቤ ሁሉ ለወላጅ ግልጽና የታወቀ ነው።

  • ራሳችንን እናሳድጋለን፦ የተሻለ እንክብካቤና ትምህርት ለመስጠት ሁልጊዜም አዳዲስ አሰራሮችን እንጨምራለን።

  • ለቤተሰብ እሴቶች ክብር አለን፦ እናንተ ልጃችሁ እንዲማርበትና እንዲያድግበት የምትፈልጉትን የቤተሰብ ስርዓትና ባህል አክብረን እናስቀጥላለን።

በማንኛውም ጊዜ መጥታችሁ እንድታዩን፣ እንድንመካከርና ለልጃችሁ እድገት አብረን እንድንቆም በደስታ እንጋብዛችኋለ

የስራ ቀናትና ሰዓት

  • የስራ ቀናት፦ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ

  • የስራ ሰዓት፦ ጠዋት ከ1፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት

ኑ እና ጎብኙን!

የልጆቻችን ውሎ፣ እንክብካቤና ትምህርት ምን እንደሚመስል በአካል መጥታችሁ እንድታዩ በደስታ እንጋብዛችኋለን።

📍 አድራሻችን፦ አያት፣ ፍሬሽ ኮርነር መንገድ፣ ዞን 6 (ፖሊስ ጣቢያው ወይም ተምር ፕሮጀክት አካባቢ)

📞 ስልክ፦ * ቢሮ፦ 011 839 0313

  • ሞባይል፦ 095 312 3266 / 094 734 9847

ፋምዝ የልጆች ማቆያ (Femeze Daycare)

የልጅዎ አስተማማኝ ሁለተኛ ቤት!

ሕፃናት በሰላም ተጠብቀው፣ በፍቅር ታቅፈውና በባህላችን ታንጸው እንዲያድጉ በትጋት እንሠራለን። ትኩረታችንም ጥራት ባለው እንክብካቤ፣ በመሠረታዊ ትምህርትና በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ነው።

የአገልግሎት አይነቶች

የሀገር ባህልና ወግ ማስተማር

የበገና ልምምድ

የቴኳንዶ ስልጠና

የልጆች ማቆያ (እንደ ፍላጎትዎ)

የልጆች አስተዳደግ ምክርና ልዩ ድጋፍ

እኛን ያግኙን

© 2026 Femeze Daycare Center. Developed by HF Digital Networks PLC