ፋምዝ (Famezs) የህፃናት ማቆያና የክህሎት ማበልጸጊያ

“የነገ ማንነት ዛሬ በየኛ ይገነባል!”


የሀገር ባህልና ወግን በጨዋታ ማስተማር

“ማንነትን፣ ኩራትንና ማህበራዊ ክህሎትን መገንቢያ” ልጆች ገና በለጋነታቸው የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ እንዲያውቁ እናደርጋለን። በተረቶች፣ በዜማዎች፣ በተውኔትና በባህላዊ ጨዋታዎች አማካኝነት ልጆች በማንነታቸው እንዲኮሩና ከሰው ጋር የመግባባት ችሎታቸው እንዲዳብር በትጋት እንሰራለን።

  • የእድሜ ክልል፦ ከ3 – 13 ዓመት

  • የጊዜ ሰሌዳ፦ በሳምንት 2 ቀን

  • ትኩረታችን፦ የኢትዮጵያ እሴቶች፣ አብሮነት፣ መሠረታዊ የፊደልና የቁጥር እውቀት።

  • ተግባራት፦ ባህላዊ ተረቶች፣ መሠረታዊ የአማርኛ ትምህርት፣ የበዓላት አከባበርና የባህል እደ-ጥበባት።

የበገና ልምምድ

“ሙዚቃ፣ ትኩረትና የውስጥ ሰላም” ልጆች በትዕግስት እንዲታነጹ፣ ትኩረት እንዲለማመዱና ስሜታቸውን በሙዚቃ እንዲገልጹ ይረዳቸዋል። ይህም ከሀገራቸው ታላቅ የሙዚቃ ታሪክ ጋር በልጅነታቸው ያስተሳስራቸዋል።

  • የእድሜ ክልል፦ ከ4 – 13 ዓመት

  • የጊዜ ሰሌዳ፦ በሳምንት 3 ቀን

  • ጥቅሙ፦ የሙዚቃ ችሎታ፣ ከፍተኛ ትኩረትና የባህል ፍቅር።

  • ተግባራት፦ የተግባር ልምምድ፣ በቡድን ዜማዎችን ማቅረብና የዜማ ስልጠና።

የተይኳንዶ ስልጠና

“ስርዓት፣ በራስ መተማመንና አካላዊ ጥንካሬ” ተይኳንዶ ልጆች ብርታት፣ ቅልጥፍናና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ያደርጋል። በጨዋታ የታጀቡና ስነ-ስርዓትን የሚያስተምሩ ስልጠናዎችን በታዋቂ ባለሙያዎች እንሰጣለን።

  • የእድሜ ክልል፦ ከ5 – 13 ዓመት

  • የጊዜ ሰሌዳ፦ በሳምንት 2 ቀን

  • ጥቅሙ፦ ጤንነት፣ ስነ-ምግባር (ዲሲፕሊን) እና ለሌሎች ክብር መስጠት።

  • ተግባራት፦ የማሟሟቂያ እንቅስቃሴዎች፣ መሠረታዊ የተይኳንዶ ስልቶችና አዝናኝ ውድድሮች።

አመቺ የልጆች ማቆያ (እንደ ፍላጎትዎ)

“ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ አመቺነቱ” ወላጆች እንደ ስራ ሁኔታዎ በሙሉ ቀን፣ በግማሽ ቀን ወይም በተመረጡ ቀናት ልጆቻችሁን እኛ ጋር በማስገባት የእለት ስራዎን በሰላም ማከናወን ይችላሉ።

  • አማራጮች፦ የዕለት ተዕለት ወይም የተመረጡ የሳምንት ቀናት።

  • ትኩረታችን፦ ደህንነት፣ ምቾት፣ ትምህርታዊ ጨዋታዎችና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ።

  • ተግባራት፦ ቁጥጥር የሚደረግበት ጨዋታ፣ የስዕልና ስራ ጥበብ እና የሥርዓተ-ምግብ ጊዜ።


የምክር አገልግሎትና የወላጆች ድጋፍ

ልጅዎን የትኛው ፕሮግራም ላይ ማሳተፍ እንዳለብዎት ከእኛ ጋር መመካከር ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ልጅ እንደ ፀባዩ የሚስማማውን ፕሮግራም እንጠቁማለን፤ ስለ አመዘጋገብና ስለ ውሎውም በዝርዝር እንነጋገራለን።


የሥራ ሰዓትና አድራሻ

የመማሪያ አካባቢያችን ንጹህ፣ ሰላማዊና ለልጆች ምቹ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። ዛሬውኑ ብቅ ብለው ይጎብኙን!

  • የሥራ ቀናት፦ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ

  • የሥራ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት (7:00 AM – 4:00 PM)

ለመመዝገብ ዝግጁ ነዎት?

  • 📞 ቢሮ፦ 011 839 0313

  • 📱 ሞባይል፦ 095 312 3266 | 094 734 9847

  • 📍 አድራሻ፦ አያት፣ ፍሬሽ ኮርነር መንገድ (ዞን 6)

Previous Post

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ፋምዝ (Famezs) የህፃናት ማቆያ ማዕከል

እውቀትን፣ ባህልንና እድገትን በአንድ ላይ!

Category

Latest posts

Contact Info

ለበለጠ መረጃና ምዝገባ

ልጅዎ የደስታ ጉዞውን ከየኛ ጋር እንዲጀምር ዛሬውኑ ብቅ ብለው ይጎብኙን ወይም በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉልን፦

  • 📞 ቢሮ፦ 011 839 0313

  • 📱 ሞባይል፦ 095 312 3266 / 094 734 9847

Edit Template

ፋምዝ የልጆች ማቆያ (Femeze Daycare)

የልጅዎ አስተማማኝ ሁለተኛ ቤት!

ሕፃናት በሰላም ተጠብቀው፣ በፍቅር ታቅፈውና በባህላችን ታንጸው እንዲያድጉ በትጋት እንሠራለን። ትኩረታችንም ጥራት ባለው እንክብካቤ፣ በመሠረታዊ ትምህርትና በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ነው።

የአገልግሎት አይነቶች

የሀገር ባህልና ወግ ማስተማር

የበገና ልምምድ

የቴኳንዶ ስልጠና

የልጆች ማቆያ (እንደ ፍላጎትዎ)

የልጆች አስተዳደግ ምክርና ልዩ ድጋፍ

እኛን ያግኙን

© 2026 Femeze Daycare Center. Developed by HF Digital Networks PLC