ልጅዎ የመጀመሪያውን ቀን በቀላሉ እንዲለምድ ምን ማድረግ አለብን?

ልጅን ማቆያ ማስገባት ለልጁም ሆነ ለወላጆች ትልቅ እርምጃ ነው። በፋምዝ የህጻናት ማቆያ፤ የልጅዎ የመጀመርያ ቀን አስደሳችና በራስ መተማመን የሚፈጥር እንዲሆን በትጋት እንሰራለን። ልጅዎ የኛ ጋር ሲመጣ ሰላም፣ ምቾትና የመማር ጉጉት እንዲሰማው እናደርጋለን።

ለወላጆች ጥቂት ምክሮች፦

  • ቀድመው ያጫውቷቸው፦ ስለ ማቆያው ውሎ፣ ስለሚጫወቷቸው አዳዲስ ጨዋታዎችና ስለሚያገኟቸው ጓደኞች በደስታ ይንገሯቸው።
  • አብረው ብቅ ብለው ይጎብኙን፦ ከመመዝገብዎ በፊት ልጅዎን ይዘው መጥተው አካባቢውን እንዲያዩትና ከመምህራኖቻችን ጋር እንዲተዋወቁ ማድረግ ትልቅ መረጋጋትን ይሰጣቸዋል።
  • ውሎውን ከቤት ይጀምሩ፦ የልጅዎን የምግብ፣ የጨዋታና የእንቅልፍ ሰዓት ቀስ በቀስ ከማቆያው የጊዜ ሰሌዳ ጋር ማመጣጠን ትልቅ መልመጃ ይሆናቸዋል።
  • የሚወዱትን ነገር ይላኩ፦ የሚወዱትን አሻንጉሊት፣ ትንሽ ብርድ ልብስ ወይም የሚወዱትን መክሰስ ይዘው እንዲመጡ ማድረግ የቤት ስሜት እንዲሰማቸው ይረዳል።
  • በራስ መተማመን ያሳዩ፦ ልጆች የወላጆቻቸውን ስሜት በፍጥነት ይረዳሉ፤ እርስዎ በማዕከላችንና በመምህራኖቻችን ላይ እምነትና ደስታ ሲያሳዩ ልጁም ያለ ስጋት እንዲለምድ ያግዘዋል።

ልጅዎን በስነ-ልቦና ማዘጋጀት፦

  • ልጆች እንደ ልብስ መልበስ ወይም አሻንጉሊቶችን ማስተካከል ያሉ ትንንሽ ስራዎችን በራሳቸው እንዲሰሩ በማበረታታት በራስ መተማመናቸውን ማሳደግ።
  • ከሌሎች ልጆች ጋር እንዲጫወቱና እንዲግባቡ በማድረግ ማህበራዊ ህይወትን እንዲለምዱ መርዳት።
  • ስሜታቸውን በነጻነት እንዲገልጹና አዳዲስ ነገሮችን ያለ ፍርሃት እንዲቀበሉ ማበረታታት።

ማጠቃለያ

አስደሳችና ሰላማዊ የመጀመርያ ቀን ለልጅዎ መልካም ቆይታ ትልቅ መሰረት ነው። በፋምዝ የህጻናት ማቆያ፤ ፍቅርን፣ ስርዓትንና አዝናኝ ጨዋታዎችን አቀናጅተን ልጅዎ አዲሱን ጉዞ በደስታና በልብ እርግጠኝነት እንዲጀምር እናደርጋለን።

ዛሬውኑ ብቅ ብለው ይጎብኙን፤ ልጅዎ የደስታ ጉዞውን ከየኛ ጋር እንዲጀምር ያድርጉ!

Previous Post
Next Post

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ፋምዝ (Famezs) የህፃናት ማቆያ ማዕከል

እውቀትን፣ ባህልንና እድገትን በአንድ ላይ!

Category

Latest posts

Contact Info

ለበለጠ መረጃና ምዝገባ

ልጅዎ የደስታ ጉዞውን ከየኛ ጋር እንዲጀምር ዛሬውኑ ብቅ ብለው ይጎብኙን ወይም በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉልን፦

  • 📞 ቢሮ፦ 011 839 0313

  • 📱 ሞባይል፦ 095 312 3266 / 094 734 9847

Edit Template

ፋምዝ የልጆች ማቆያ (Femeze Daycare)

የልጅዎ አስተማማኝ ሁለተኛ ቤት!

ሕፃናት በሰላም ተጠብቀው፣ በፍቅር ታቅፈውና በባህላችን ታንጸው እንዲያድጉ በትጋት እንሠራለን። ትኩረታችንም ጥራት ባለው እንክብካቤ፣ በመሠረታዊ ትምህርትና በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ነው።

የአገልግሎት አይነቶች

የሀገር ባህልና ወግ ማስተማር

የበገና ልምምድ

የቴኳንዶ ስልጠና

የልጆች ማቆያ (እንደ ፍላጎትዎ)

የልጆች አስተዳደግ ምክርና ልዩ ድጋፍ

እኛን ያግኙን

© 2026 Femeze Daycare Center. Developed by HF Digital Networks PLC